“በህዳር 14 ማለዳ ሰዎች ቤታችን ድረስ መጥተው ባለቤቴን ሁከት ፈጥሯልዕ በሚል ወሰዱት። ማመን አቃተኝ። ወዲያውኑ ፖሊስ ጣብያ ሄጄ የት ታስሮ አንዳለ ስጠይቅ አዲስ ማመልከቻ አግቢ የሚል ምላሽ ተሰጠኝ። ሳምንታት ወደ ወራት ሲቀየሩ ባለቤቴ በህይወት ይኑር አይኑር አንዳችም አዲስ ነገር አልሰማሁ። እኔና ልጆቼ የምንተዳደረው ባለበቴ ቀለም ስራ ሰርቶ በምትከፈለው ነበር። ጎረቤቶቼ የቤት ስራ እስካገኝ ረድተውን ቆየን። ልጆቼ ችግር በጭንቀት ሆኖባቸው ትምህርታቸውን መከታተል ባለመቻል ሱቅ ውስጥ ለመቀጠር ተገደዱ። ልጆቼ ተመርቀው ራሳቸውን አንዲችሉ እንጅ ይሄ ይመጣል ብዬ አላዘጋጀዋቸው። ግንቦት አጋማሽ ቢመለስም የት ይህን ጊዜ አንዳሳለፈ ሊነግረኝ ፈቃደኛ አልነበረም፤ እነዝያም ትምህርት ቀጥሉ ሲባል አልሰማ ብለው አሉ።”